News anchor

Alexandria, VA
Joined August 2011
ሩሲያዎች ግን ብልጥ ናቸው። በ1ቢሊዮን ዶላር የጦር አውሮፕላን ሸጠው ከአብይ አህመድ የመደመር መጽሀፍ ገዙ። የዚህ ሰው ጅልነትና ድንቁርና ግን ወሰን የለውም። እንደሰማሁት SU 35 የጦር ጄት ማብረር የሚችል አንድ ፓይለት ብቻ ነው ኢትዮጵያ ያላት። እነዚን 12 ጄቶች የሚያበሩ ባለሙያዎችን ለማሰልጠን በትንሹ ከሁለት ዓመት በላይ ያስፈልጋል። ከዚህ የጦር ጄቶች ሸመታ የተረፈን የአብይ አህመድ ጉራ ብቻ ነው። መጽሀፉን በሩሲያ ቋንቋ ለማስተርጎምና ለማሳተም በሚሊየን ብሮች ወጪ ተደርገዋል። ሩሲያዎች አብይ አህመድን እንደ አሻንጉሊት ይጫወቱበታል። ከኢትዮጵያ ህዝብ ጉሮሮ በተነጠቀ ገንዘብ መልሶ የኢትዮጵያን ህዝብ ለሚጨርሱ የጦር ጄቶች 1ቢሊዮን ዶላር(187 ቢሊየን ብር) ሞጭልፈው ለአብይ አህመድ ኢጎ ማከኪያ መጽሀፉን ገዙለት። የሽያጩ ዋጋ የአስተርጓሚዎችን ክፍያና የህትመቱን ወጪ እንደማይሸፍንም እየተነገረ ነው። አንድ ቁልፍ ጉዳይ ግን እንዳይዘነጋ። ''ንጉስ በሰራዊት ብዛት አይድንም'' - ይሔው ነው!
15
7
42
1,375
ዛሬም ጃዋር መርዙን ረጭቷል። የአርሲውን ጭፍጨፋ ተሳልቆበታል። እንደለመደው መንግስት ባስታጠቃቸው የአማራ ተወላጆችና በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት እንዲሁም በኦህዴድ ሚሊሺያዎች መሀል ግጭቶች እንዳሉ በመግለጽ እጅግ አስነዋሪና በወንጀልም የሚያስጠይቅ ቃለመጠይቅ ለዶቼቬሌ(አዲሱ ተደማሪ ሚዲያ) ሰጥቷል። በእውነት ይህን ሰው ተረባርቦ ለህግ እንዲቀርብ መደረግ ያለበት ነው። የአርሲው ጭፍጨፋ የሱ ''99በመቶ ሙስሊም ነው፡ ሌላ ካለ በሜንጫ አንገቱን ነው የምንቆርጠው'' እንዲሁም ''ኢትዮጵያ አውት ኦፍ ኦሮሚያ'' ንግግሮች ውጤት መሆኑ ግልጽ ጉዳይ ነው። ይህ ሰው ከአብይ አህመድ የሚለየው በውጭ ሀገር ስለሚኖር ብቻ ነው። ዛሬ ወለጋ ላይ ከ80 በላይ አማራዎች በገጀራ ተከትክተው ተገድለዋል። ጃዋር የወለጋውን የቅርብ ጊዜ ጭፍጨፋ ፊሽካ ነፍቶ ስለማስጀመሩ በብዙ ማስረጃዎች አስደግፎ መግለጽ ይቻላል። ይህ ሰው እረፍት የለውም። እንቅልፍ አይተኛም። አብይ የጦር ጄት ገዛ ብሎ ኤሊፖፕ እንደተገዛለት ህጻን ሲቦርቅ ነው የዋለው። እጅግ አደገኛ፥ ደም የጠማው፥ እርኩስ መንፈስ የተጠናወተው ግለሰብ ነው። ይህን ሰው ተረባርቦ ከጥላቻና ዘር ተኮር ንግግሮቹ እንዲታቀብ መደረግ አለበት። በነገራችን ላይ ዶቼቬሌ የአማርኛው አገልግሎት መደመሩን የሚያሳዩ ነገሮችን እየታዘብኩ ነው። በተለይ ይሄ ጃዋርን ቃለመጠይቅ ያደረገለት ታምራት ዴንሳ የሚባል ''ጋዜጠኛ'' ጣቢያውን የኦህዴድ/ብልጽግና ልሳን አድርጎታል። የህወሀቱ ጄነራል አብረሃም ድንኩል ተከቧል ብሎ የፌስቡክ ቧልት ይዞ ዶቼቬሌን በመሰለ ዓለምዓቀፍ ሚዲያ ላይ ሲበጠረቅ ስሰማው ድንግጥ ነው ያልኩት። ቤቱን ስለማውቀውና ለአጭር ጊዜም ቢሆን ስለሰራሁበት። ኋላ ላይ የሰራቸውን ስቃኛቸው የሚያስተላልፋቸው ዜናዎች እንዳለ ፌስቡክ ላይ ጥንባቸውን የጣሉ ያልተጣሩና ያልተገሩ መረጃዎችን ምንጭ እያደረገ የሚያቀርባቸው ነው። እነነጋሽ መሀመድ ምን ነካቸው? ሂሩት መለስ እንዴት ዝም አለች? ሸዋዬ ለገሰ ባለችበት ሚዲያ ነው ይህ የኦህዴድ/ብልጽግና ካድሬ የሚፈነጨው? ያሳዝናል።
55
3
98
6,697
''የቅዱሳን ፓትርያርኮችና የብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት መታሰቢያ በዓል ለወደፊቱ ተጠናክሮና በሚገባ መንፈሳዊ ክብር እና ሥርዓት መሠረት ትኩረት ተሰጥቶት እንዲከበር ጉባኤው ወስኗል።'' ከቅዱስ ሲኖዶሱ ውሳኔዎች አንዱ ነው። ወቸ ጉድ!
17
3
55
8,205
ቢዘገይም ምርቱ ደርሷል። ሂድና ሰብስብ!
170
12
278
9,752
የ'no more synod' ንቅናቄ ሊጀመር መሆኑን የሚያሳዩ አንዳንድ እንቅስቃሴዎችን እያስተዋልኩ ነው። በእርግጥ ሲኖዶሱ ባይኖር ኦርቶዶክሳውያን ምን ይጎዳሉ? ጥያቄው መነሳቱ ተገቢና ወቅታዊ ነው። የአህያ ባል ከጅብ አይስጥልም የሆነው ቅዱስ ሲኖዶስ፥ ከ60 በላይ ምዕመናን ለተገደሉበት የአርሲው ጭፍጨፋ ያወጣው የሀዘን መግለጫ የሲኖዶሱን መኖር እርባና ቢስ የሚያደርገው ተጨማሪ ማስረጃ ነው። አሁንም አብይ አህመድን 'አማልደን' የሚሉበትን መግለጫ ማውጣታቸው በትክክልም ''ሲኖዶስ አያስፈልግም'' የሚለውን ገና ዳዴ እያለ ያለን ንቅናቄ ተገቢ ያደርገዋል። የሀዘን መግለጫው አብይ አህመድን የሚለማመጥ ነው። ሲኖዶሱ ንብረቱን ከሰረቀው ሌባ ጋር ንብረቱን እንዲያፋልገው ራሱኑ ሌባውን የሚጠይቅበት መግለጫ በግፍ በተገደሉት ምዕመናን ደም ላይ መሳለቅ እንጂ ሌላ ትርጉም የለውም። ጥቁር ልብሰ ትክህኖ የመልበሳቸው መንፈሳዊ ትርጉም ግልጽ ነበር። የእነሱ የእምነት ተልዕኮ በሞት ደጃፍ ቆመው ስለልጆቻቸው የሚጸልዩ የሚለምኑ እንዲሆኑ ነበር። ከጥቂቶቹ አባቶች በስተቀር አብዛኞቹ ከቤተክህነት ይልቅ ለቤተመንግስት ቃል የሚገዙ ናቸው። ከፈጣሪ ይልቅ የአብይ ድምጽ ያስፈራቸዋል። ከእግዜብሔር ቁጣ፥ የአብይ ፊት ማጥቆር ያንበረክካቸዋል። ከእነዚህ አባቶች ስለምን መፍትሔ እንጠብቃለን?! ልብ ያለው ልብ ይበል!
104
6
268
20,797
የሆነ ነገር በቃ ልክ አይደለም። ኢትዮጵያ በጽኑ ታማለች። ይሄ እየሆነ እኛ ምን እያደረግን ነው? እንደተለመደው ወጥተን እየገባን? ምግብ እየበላን ውሃ እየጠጣን? ህይወት ቀጥላለች ማለት ነው? ምንም እንዳልተፈጠረ የዘውትር ተግባራችንን ቀጥለነዋል? እውነት ምን ነካን? የብልጽግና ደጋፊዎች፥ እዚህ መንደር እየመጣችሁ ይህን ግፍ ምክንያት የምታለብሱ ጨካኞች፥ ሁላችሁም ነገ ትጠየቃለችሁ። ይሄም ጊዜ ያልፋል።
521
32
696
18,377
ደግሞ ይመጣል እንዳልኩት መጣ። ጥቁር መነጽሩን አድርጎ፥ እየተዘባነነና ፊደል እየቆጠረ ''ጽምዶ አርሲ ላይ ንጹሃንን ገደለ'' የሚል ሀተታ ይዞ ገጭ ይላል የሚል ከጥርጣሬ የዘለለ - ከእርግጠኝነት መለስ ያለ ግምት እየሰጠሁ ነበር - ትላንት የአርሲውን ጭፍጨፋ እንደሰማሁ። ግምቴ መሬት ጠብ አላለም። የኦቦ አዱኛ ልጅ፥ ጃል ሃይሉ የህንድ አክተር መስላ፥ ግዳይ እንደጣለች፥ ደረቷን ነፍታ፥ የሚዲያ ማይኮችን ከፊቷ ደርድራ ከች አለች። አሰብን ነጻ አውጥታ የተቆጣጠረችና ያንን ልታበስር የመጣች ነው የምትመስለው። እንደገመትኩትም ''ጽምዶ በአርሲ የሃይማኖት ጦርነት ከፍቶ አከሸፍነው'' አለ። አይኑ አይርገበገብ (ወይ ጉድ?!አይኑን በየት አየሁት? መጣንጥር አድርጎ የለ? ምጽጽ) ሃይልሻ ሰሞኑን ኦቦ ጌታቾ መርዳሳ( ረዳ) ያለውን አልሰማህም? ''ጽምዶ የፈረሰው እንደተመሰረተ ነው'' ብሏል እኮ?! ታዲያ የትኛው ጽምዶ ነው አርሲ የተከሰተው?
98
7
215
41,024
ብልጽግናዎች ግን እንቅልፍ ተኝተው ያድራሉ? ይሄን ሁሉ መከራ፥ መዓት፥ ግድያ፥ ዕልቂት ሀገሪቱን ከዳር እስከዳር አኬልዳማ አድርገው፥ ይህን የሚያደርግን ስርዓት እየደገፉ፥ ማታ ሲመሽ እንደእኛው አልጋ ውስጥ ገብተው ይተኛሉ? ምን ዓይነት ፍጡር ናቸው ግን? እኔስ አልቻልኩም። የአርሲውን ጭፍጨፋ እንዴት ለአፍታም ከአእምሮዬ ውስጥ ላውጣው?
82
10
211
12,109
ሁለት ቪዲዮችን አየሁ። ከዚያም የአብይን የዕለቱ ውሎ የሚያሳይ አንድ ፎቶግራፍ ተመለከትኩ። ምን ሀጢያት ብንሰራ ነው ግን እዚህ ሰው እጅ ላይ የጣለን? ቪዲዮዎቹ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ስለተለቀቁ በቀላሉ የሚገኙ ናቸው። በአርሲ ሻርካ 47 ኦርቶዶክሳውያን ተገድለው አስክሬናቸው በየሜዳው ላይ ጨርቅ ለብሶ ይታያል። በርካታ አስክሬን ደግሞ በአንድ ቤት ውስጥ ይገኛል። በሌላኛው ቪዲዮ ላይ ደግሞ 36 አስክሬን በአንድ ጉድጓድ ሲቀበር የሚታይበት ነው። ይዘገንናል። ስሜትን ይቆነጥጣል። አጥንት ድረስ ዘልቆ በሚገባ ብርቱ የሀዘን ስሜት ውስጤ ይንቀለቀላል። ወዲህ ደግሞ አብይ አህመድ ባህር ዳር ላይ ከኬኒያው ምክትል ፕሬዝዳንት ጋር ኳስ ይጠልዛል። እንዴት ያለ ጨካኝ ሰው ነው? ባለፈው በምርጫው ሰሞን አርሲ ተመሳሳይ ግድያ ሲፈጸም ፓርላማ ላይ ወጥቶ፥ አይኑን እያጉረጠረጠ ''ምርጫውን ለማደናቀፍ የተሸረበ ሴራ ነው'' ሲል እየደነፋ ተናገረ። አሁንስ ምን ለማደናቀፍ ነው 47 ኦርቶዶክሳውያን የተገደሉት? ርህራሄ፥ ሀዘኔታ እንዲህ ከአንድ ሰው ውስጥ ተንጠፍጥፎ ያልቃል ማለት ነው? ቤተክርስቲያኗ አፏ ታሽጓል። አብይ አህመድ በደህና ጊዜ ሽባ አድርጓታል። ልጆቿ ሲገደሉ ትንፋሿ እንኳን እንዳይሰማ ተደርጋለች። እነአቡነ ሳዊሮስ ከአዳነች አቤቤ ጋር ነገር አለማቸውን እየቀጩ ነው። አይሰሙም፥ አይለሙም። የዚህች ቤተክርስቲያን ሁኔታ እጅግ የሚያሳስብ ነው። አቤት ግፍ! ምን ይሻላል?! ለሞቱት ነፍስ ይማር፥ ለቤተሰቦቻቸው መጽናናትን እመኛለሁ!
111
8
202
13,557
ይህ ሰው ሀገሪቱን እያፈራረሳት ነው ስንል ባዶ ጩኸት የሚመስላቸው ሰዎች አሁንም ከእንቅልፋቸው አልነቁም። ሞያሌ ላይ የሚታየው አስጨናቂ ትዕይንት የአብይ አህመድ የእጅ ስራ ውጤት ነው። ሰውዬው የሀገር ማፍረሺያ መዶሻ ይዞ የሚዞር እንደሆነ በሚያደርጋቸውና በሚናገራቸው በግልጽ መረዳት ይቻላል። ኢትዮጵያ በአራቱም ማዕዘናት ብርቱ ትኩሳት እያሰቃያት ነው። በትግራይና በአማራ ያለውን የለየለት ጦርነት እናቆየውና በሌላው የኢትዮጵያ ክፍል ባለፉት አራት ቀናት የሆኑትን ብቻ ብንመለከት 'ኢትዮጵያ' ሀገር ወይስ የአርማጌዲዮን ምድር - የሚል ጥያቄ አንስተን ወዲያውኑ መልስ የምናገኝበት ጉዳይ ነው። ቡርጂ ገበሬዎች ተገድለዋል፥ ፊንጫ ስኳር ፋብሪካ ሰራተኞች በጥይት ረግፈዋል፥ ወለጋ ከ200 በላይ ዜጎች ተጨፍጭፈዋል፥ ጉራጌ የማያባራው ግድያ ሰሞኑንም ተባብሶ ቀጥሏል፥ ምስራቅ አርሲ ኦርቶዶክሶች በብዙ ቁጥር መገደላቸው ታውቋል፥ ጋምቤላ ነፍሷን ሲጥ ያደረገ ውጥረት ውስጥ ናት፥ በደቡብ ኢትዮጵያ ኮንሶ ቀጠና መፈናቀል ግድያና መንደሮች መቃጠል ተራ ክስተት ሆኗል፥ ቤንሻንጉል ጉምዝ የሰው ልጅ ቄራ መሆኑን ከሰሞኑም በተፈጸሙ ግድያዎች ተረጋግጧል፥ አሁን ደግሞ ሞያሌ እየነደደች ነው። ከዚህ በላይ ሀገር መፍረስ እንዴት ሊገለጽ ይችል ይሆን? ስንት ሰው እስኪያልቅ ይሆን ለዚህ ሰው በጥፋት መንገዱ እንዲቀጥል የሚፈቀድለት?
71
4
146
12,505
BBC News Amharic ያወጣውና ህወሀትን የተመለከተው ዘለግ ያለ ዘገባ መሬት ላይ ካለው እውነታ ጋር የሚጣጣም አይደለም። ለብልጽግናው አገዛዝ የአሸናፊነት ዋንጫውን የሰጠው ይህ ዘገባ የሶስት ሰዎችን አስተያየት በዝርዝር ያቀርባል። የቀድሞ የህወሀት የደህንነት ሰው የነበረና እዚህ አሜሪካን ሀገር የሚኖረው አቶ ብስራት አማረ የተሰኘው ግለሰብ ህወሀትን ሞቶ የተቀበረ፥ አስክሬኑ የሚንከላወስ፥ የትግራይ ህዝብ እክ እንትፍ አድርጎ የተፋው፥ ሁሉ ነገር ያበቃ ያከተመ አድርጎ የገለጸበት ሁኔታ የሰውዬውን የቀደመ ማንነት ለሚያውቁ ብዙም የሚደንቃቸው አይደለም። ባለፉት ስድስት ቀናት በትግራይ ምድር እየሆነ ያለውን በተጨባጭ መረጃ ሂደቱን ለሚከታተል ሰው ደግሞ አቶ ብስራት አማረ የትኛው ፕላኔት ላይ እየኖሩ ነው የሚል ጥያቄ ሊያነሳ ይችላል። ሌላኛው የፖለቲካ ታዛቢ ተብለው አስተያየታቸው በስፋት የቀረበላቸው ዶ/ር ጌትዬ የተባሉትም ሰው ጭልጥ ያሉ የብልጽግና ደጋፊ እንጂ ነጻ ምሁር ሆነው አላገኘኋቸውም። ዶ/ር ጌትዬ ጭራሹኑ ትብብር ለህልውናን አፈር ከድሜ ሲያስግጡት የሰውዬውን ገለልተኛ ምሁርነት በትልቁ ጥያቄ ውስጥ እንዳስገባ አስገድዶኛል። ሶስተኛው ምሁር ዶ/ር ደረጀ ሀዋስ በተሻለ ሁኔታ ሚዛናዊ ሆነው አግኝቼአቸዋለሁ። በአጭሩ የBBC News Amharic ረዘም ያለ ዘገባ ሰንካላ ነው። ድምት፥ እሽት ተደርጎ የተሰራ አይደለም። በቆዩና ባረጁ መረጃዎች መነሻነት እንዲሁም በግል አቋምና ፍላጎት ላይ ተመርኩዘው ''ምሁራዊ'' በሚል ጭምብል የቀረበ ሚዛናዊነት የጎደለው ዘገባ ነው። መሬት ላይ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ ፈጽሞ አያሳይም። ከዚህ ሚዲያ እንዲህ ዓይነት ቀሽም የሆነ ዘገባ አልጠብቅም። ለሰዉ ትክክለኛ የሆነ ምስል የማይከስት፥ የአንድ ወገንን አቋም የሚያጎላ ዘገባ ትርፉ ሚዲያውን ተመልካች ያሳጣዋል። ብልጽግና በቂ የሆኑ ሜይንስትሪምና ዲጂታል ሚዲያዎች አሉት። የብልጽግና ፕሮፖጋንዳ ሰዉን መቆሚያ መቀመጪያ አስጥቷል። የኢትዮጵያ ህዝብ የተደበቁ ድምጾችንም መስማት ይፈልጋል። ከBBC News Amharic ቢያንስ የተወሰኑ ሚዛናዊነትን የጠበቁ የተደበቁ ድምጾችን እንጂ የምንጠብቀው የብልጽግናውን ጩኸትማ እስኪያንገሸግሸን እየተጋትነው ነው። በነገራችን ላይ የ43 ዓመት የCNN ቆይታዋን ያጠናቀቀችው ታዋቂዋ ጋዜጠኛ Christiane Amanpour በስንብት መልዕክቷ ያለችው ለእኛ ጋዜጠኞች ትልቅ ትምህርት ነው ''Remember: Always be truthful, not neutral."
59
11
127
17,716
ብልጽግናዎች የማርኮ ሮቢዮ የአንድ ደቂቃ ንግግር የፈጠረባቸው ስካር እስከአሁን አልቀቃቸውም። ዛሬ ሀንጎቨር ላይ ናቸው። ''በኢትዮጵያ ክብር ከመጡ አንገቴ ይቀላታል እንጂ አይሆንም'' የሚል ቲያትረኛ መሪያቸው የተናገረውን ዘንገተውት ከነጩ ቤተመንግስት የሚነገረውን እንደፈጣሪ ቃል ተቀብለውት በደስታ አቅላቸውን ስተው ማየት የሰሞኑ አስደማሚ ትዕይንት ነው። እነዚህ የአንድ ፋብሪካ የአስተሳሰብ ምርቶች ከማርኮ ሮቢዮ ንግግር ውስጥ ''አዲስ አበባ በድሮን ተመታለች'' የሚል ነገር እንዳለም የዘነጉ ይመስላሉ። በተደጋጋሚ አዲስ አበባ ጥቃት ደርሶባታል እያልን ስንገልጽ ሲያጣጥሉና ሲያበሻቅጡ እንደከረሙ ረስተውት ወይስ ከነጩ ቤተመንግስት እስኪመጣ እየጠበቁ ነበር? ስለማርኮ ሮቢዮ አጭር አስተያየት ሰማንያ ገጽ ትንታኔ ከመጻፍ በፊት የሚቀድመው 'አዲስ አበባ በድሮን ተመታች' የሚለውን ማመናቸውን ቢገልጹልን ጥሩ ነበር። የቀረው እዳው ገብስ ነው። የዲፖሎማሲ ጉዳይ ነው። እንደምታውን ለመተንተንም ሆነ ለመበየን ትንሽ መሬት ረግጦ ማሰብና መረዳት ይጠይቃል። የማርኮ ሮቢዮን አስተያየት እንደህልም የፈቱ፥ አዋቂ ጋር ሄደው ያስመረመሩ፥ መጽሀፍ ገላጭ ጠይቀው ውስጠ ወይራ ትርጓሜውን ይዘው የመጡ የብልጽግና መንደር ሰዎች መኖራቸውንም ታዝበናል። ይህ ሁሉ ስቃይ ለምን እንዳስፈለገ ግራ የሚያጋባ ነው። ከዚህ በላይ ክሽፈት ምን አለ? ያልተጻፈ ማንበብ የብልጽግና ሰዎች መለያ ባህሪ ነው። ቆርጦ መቀጠል የተካኑበት ልዩ ስጦታቸው ነው። አዲሱ የማህበራዊ ሚዲያ መሪያቸው ደግሞ ለይቶለት ነጩን ጥቁር ለማለት ቅንጣት ታክል ሀፍረት የማይሰማው መሆኑን በተደጋጋሚ እያየን ነው። ፌክ ዶክመንት በማሰራጨት፥ ሀሰተኛ መረጃዎችን በመለጠፍ፥ ያልተጻፈ አንብቦ ያንንም ለተከታዮቹ በማካፈል የውሸት ቋት፥ የፌክ መረጃዎች ማምረቻ ማሽን ሆኖ አርፏል። የትብብር ለህልውና ለማርኮ ሮቢዮ የሰጠውን ምላሽ እንኳን እንዴት አድርጎ ሀሳቡን አወላግዶና ገልብጦ እንዳቀረበ መታዘብ ይቻላል። ይህ ሰው የመረጠውን የመደገፍና የደበረውን የመንቀፍ መብት አለው። ሀሰተኛ መረጃ ማሰራጨትና ያልተጻፈ አንብቦ ተከታዮችን ማሳሳት ግን በምድር ወንጀል ነው፥ በሰማይ ደግሞ ያስቀስፋል። በስብሼለሁና ዶፍ ዝናብ አልፈራም ማለት መብት እንደሆነ ሁሉ ተጠያቂነትንም የሚያስከትል መሆኑን መዘንጋት አይገባም። በማርኮ ሮቢዮ አጭር አስተያየት ሰማይን እየረገጡ ከመጨፈር በፊት ግን ''የአዲስ አበባውን የድሮን ጥቃት'' አምነው ተቀብለውት ከሆነ ይቅርታ ያስፈልገናል። ሰው ከሆኑ፥ ህሊና የሚባለው ትንሹ ፈጣሪ ከውስጣቸው ካለ፥ 'ያጣጣልናችሁና ያበሻቀጥናችሁን ይቅርታ እንጠይቃለን' ይበሉ። ሌላው ነገር ይደረስበታል።
51
4
165
12,700
የአንከር ሚዲያ ደርቢ ዛሬ በዋሽንግተን ዲሲ 3PM በኢትዮጵያ ምሽት 4 ሰዓት በቀጥታ
16
3
44
8,091
አሁንም ይሳደባል አሉ። እኔ እንኳን ስድቡን እሱንም እስከመፈጠሩም ረስቼዋለሁ። ምኑ ይታወሳል?! ሰው በማወቃችሁ ተጸጽታችሁ ታውቃላችሁ? እንደዛ ዓይነት ሰው ነው። በያኔው ዘመን በእሪ በከንቱ ኮማሪቶች፥ ካቲከላ ሻጮች ጉብዝናቸው የሚለካው፥ ጥንካሬያቸው የሚገለጸው፥ ሰውም የሚያከብራቸው በስራቸው ውጤታማነት፥ በትጋትና ለሰው ልጅ ባላቸው መልካም ቀረቤታ አልነበረም አሉ። በቃ! ስድብን በዓይነት ዓይነቱ የምታዥዶደጉድ፥ አላፊ አግዳሚውን በብልግና ቃላት የምትዠልጥ፥ ወገቧን ይዛ ጣቷን ቀስራ እየተውረገረች በፊቷ የቆሙትን፥ በነገር የነካኳትን ሙልጭ አድርጋ በስድብ የምታጥረገርግ ከሆነ እሷ በቃ ሰፈር መንደሩ ይሰግድላታል። ያከብራታል። እናም ስድብ ወሰን ማስከበሪያ፥ ድንበር ማስጠበቂያ፥ ሌሎችን ማስገበሪያ ትልቁ መሳሪያ ነው አሉ። አሉ ነው እንግዲህ። እዚህ ሰፈርም በስድብ ኮሌጅ ያጠናቀቁ፥ በብልግና ዲግሪያቸውን የሰሩ፥ በጋጠወጥ ባህሪያቸው ዶክተሬት የጫኑ እንዳሉ ይታወቃል። ግን ደግሞ አንድ ሰው አለ። እሱ ይለያል። በስድብ የኦሎምፒክ ውድድር ቢኖር ኢትዮጵያ ሁሌም ወርቅ የምታገኝበት፥ አፉን በብልግና ቃላት የፈታ፥ ስድብን እንደወተት በጡጦ ሲጋት ያደገ፥ አንተን ካሳደገ የገደለ ጸደቀ እያሉ የሰፈር እናቶች እየረገሙት የጎረመሰና የጎለመሰ፥ እንደእሪ በከንቱ ኮማሪቶች ወገቡን ይዞ እየተውረገረገ የብልጽግና ተቃዋሚዎችን አንድ በአንድ ስም እየጠራ የሚሳደብ፥ አንድ ሰው አለ። የሚገርመው ከእሪ በከንቱ ተሳዳቢ ኮማሪቶች በስድብ ብቃቷ ማንም የማይደርስባት፥ ሁሉንም ያስከነዳች አንድ ስመጥር ተሳዳቢ ነበረች። አንዳንድ ከሚስቶቾቻቸው የተጣሉ ባሎች ገንዘብ እየከፈሏት የምትሰድብላቸው ይህቺው ኮከብ ተሳዳቢ ናት። ''እንኳን ተከፍሎኝ ሳይከፈለኝም ስሳደብ ኖሬ የለ?!'' ትላለች ዋጋ ስትደራደር። ይህኛው የማህበራዊ ሚዲያ ተሳዳቢም ለብልጽግና የሚሰጠው ሌላ አገልግሎት የለም። መሳደብ፥ ያልታረመና ያልተገራ አፉን ይዞ ትልልቅ ሰዎች ላይ መፈናጠጥ፥ በቃ! እነብርሃኑ ጁላ ስደብልን፥ አዋርድልን ካሉት አካውንቱ ውስጥ የሚገባውን ብር ሳይጠብቅ ነው የስድብ አርጩሜውን የሚያወናጭፈው። ለሱ ህይወት ይሄ ነው። እንጀራው ነው። ''ስራህ ምንድን ነው?'' ተብሎ ቢጠየቅ የሚመልሰው ምን ይሆን? በነገራችን ላይ ብርሃኑ ጁላም እልም ያለ ተሳዳቢ ነው። አንድ ጊዜ ቃለመጠይቅ ሳደርግለት እጅግ ነውር የሆኑ ስድቦችን ተጠቅሞ ነበር። ለወንበሩ ክብር ስል ኤዲት አድርጌ አውጥቼዋለሁ። አሁን እነብርሃኑ ጁላ በራሳቸው መሳደብን ቀንሰዋል። ይህንን የስድብ ጥማታቸውን የሚወጣላቸው ሰው ቀጥረዋል። ደምወዝ ይከፍሉታል፥ እሱም የስድብ አቁማዳውን ሸክፎ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ይወጣል። እናቱ እንዴት ይሸማቀቁበት ይሆን? ቤተሰቦቹ እንዴት ያፍሩበት ይሆን? ለነገሩ ቆንጥጠው ቢያሳድጉትና ገብረገብነት ቢያስተምሩት ኖሮ እንዲህ ዓይነት በስድብ የበለጸገ ልጅ ባልኖራቸው ነበር። በል ደግሞ እንዲህም ተባልኩ ብለህ ከኮሮጆህ ውስጥ ያልተደጋገሙ ስድቦች ካሉ ፈልገህ ስደበኝ። በነገራችን ላይ ለዚህ ጀብራሬም ሆነ መሰል የስድብ ሙያ አቻዎቹ የማስታውሳቸው ነገር ቢኖር 'ስድብ የተሳዳቢውን እንጂ የሚሰደበውን ሰው ማንነት አይገልጽም' የሚል ነው። ከገባችሁ እንደቁምነገር ውስዷት። ባይጠቅማችሁ እንኳን አይጎዳችሁም። ስሙን ያልጠቀስኩት ለስሙ ካለኝ ክብር ነው። በዚህ ስም የሚጠሩ ብዙ መልካም ሰዎችን አውቃለሁና!
40
2
144
22,924