በቅድስት ቤተክርስቲያን ላይ የሚፈጸመው ግፍና የልጆቿ መጨፍጨፍ እየጨመረ ቢመጣም ቤተክርክስቲያንን የሚያስተዳድሩ አባቶች መከራውንና ጭፍጨፋውን ለማስቀረት መሥራት ባለመቻላቸው ምእመኑ ተደራጅቶ ራሱንና ቤተክርስቲያንን እንዲጠብቅ እናሳስባለን።
ቤተክርስቲያንን በፖለቲካዊ ሴራ ለማዳከም ሲሠራ የቆየው ገዢው መንግሥት አሁን በተለያዩ አካባቢዎች በተለይም በኦሮሚያ ክልልና በአማራ መምህራንንና ምእመናንን በመጨፍጨፍና ቅዱሳት መካናትን በከባድ መሣሪያ በማውደም ሊያጠፋት እየሠራ ይገኛል።
ዜና ዕረፍት
ብፁዕ አቡነ ሰላማ ዛሬ መስከረም ፲፰ ቀን ከዚህ ዓለም ድካም ዐረፉ። ብፁዕ አባታችን ባደረባቸው ህመም ምክንያት በአዲስ አበባ ሀሌሉያ ሆስፒታል በህክምና ላይ እንዳሉ ነው ከዚህ ዓለም ድካም ያረፉት።
የብፁዕነታቸው በረከት ይደርብን!
እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የትንሣኤ እና የዕርገት በዓል በሰላምና በጤና አደረሰን አደረሳችሁ።
ሰላም ለኪ ማርያም እመ አምላክ ፤ ወልድኪ ይጼውዓኪ ፤ ውስተ ሕይወት ወመንግሥተ ክብር ።
"ወሪዶሙ እምደብር እምደብረ ታቦር ፤ አዘዞሙ ኢይንግሩ ዘርእዩ በደብር ፤ እስከ አመ ይትፌጸም በዕድሜሁ" ቅዱስ ያሬድ
እግዚአብሔር አምላካችን ብርሃነ መለኮቱን፣ ክብረ መንግስቱን ለገለጠበት በዓለ ደብረ ታቦር እንኳን አደረሰን አደረሳችሁ !
ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በወቅታዊ አገራዊ ጉዳይ ዙሪያ የተላለፈ የሰላም መልዕክት፧
***************************************
በደብረ ኤልያስ በሚገኘው ጥንታዊ ገዳም ላይ የመንግሥት ኃይሎች ከፍተኛ ጉዳት አድርሰው ከ570 በላይ ንጹሐን መጨፍጨፋቸውን የአውሮፓው ድርጅት ECLJ ገልጿል።በገዳሙ ውስጥ ከ1 ሰው በቀር በሕይወት የተረፈ አለመገኘቱን ከዚህ ቀደም መዘገባችን ይታወሳል
570 victimes, c’est le bilan de la dernière attaque d’envergure militaire perpétrée par le Gouvernement éthiopien contre le monastère de Debre-Elias. Un événement d'une grande violence contre l’Église orthodoxe qui n'est pas isolé en #Ethiopie :
eclj.org/religious-freedom/u…
"ቤተክርስቲያኒቷ ውስጥ ባልተጠበቀ እና ባልተለመደ ሁኔታ ብቅ ብቅ ሲሉ የሚታዩት ራስን በራስ የመሾም አባዜ መገታት አለባቸው፤ ማንኛውም ችግር በውይይት፣ በምክክር እና የተበደለውንም በመካስ መፈታት ይገባዋል ብለዋል።"
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ
EOTC News retweeted
The Ethiopian quest to re-create and save ancient manuscripts and legacies of the now persecuted Orthodox Tewahedo Church!
Inspiring to see scholars and the faithful at the Hamere Berhan Institute in Addis working to replicate centuries-old manuscripts and sacred artwork. #EOTC
"ልዩ ሦስት የምትሆን አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ የሚፋቀሩ የክርስቶስ ወገኖች የሚሆኑ ሕዝብህን በሰማያውያንና በምድራውያን በረከት ባርክ...የቅድስት ቤተክርስቲያንህንም ደጆች በምሕረትና በሃይማኖት እንዲከፈቱ አድርግልን፡፡"
--ጸሎተ ቡራኬ--
በትግራይ ክልል ሐምሌ 9 ይደረጋል የተባለው የኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ ሕገ ቤተ ክርስቲያንን ያላከበረ፣ አንድነቷን የሚጎዳና በጦርነት የተጎዳውን ገዳማቱና አብያተ ክርስቲያናቱ የተጎዱበትን ሕዝብ የማይጠቅም በመሆኑ እንዲቆም ቅዱስ ሲኖዶስ ጠይቋል፡፡
የሰሜኑ ጦርነት ዋነኛ ተዋናዮች እርቅ ፈጽመው በኅብረት በቆሙበት በዚህ ወቅት የሰላምና የእርቅ ሰባኪ የሆነችውን ቅድስት ቤተክርስቲያንን ባልዋለችበት በመክሰስና ከጠላቶቿ ጋር በማበር ለመከፋፈል መሥራት ትልቅና ታሪካዊ ስሕተት ነው።
የቅድስት ቤተክርስቲያን ጠላቶች ቤተክርስቲያንን ከሰሜኑ የአገራችን ክፍል ለማሰደድ እጅግ ከፍተኛ ሥራ ሠርተዋል። በዚህም በቅዱስ ፓትርያርኩ ላይ በር ዘግተው በመጥፋት በቤተክርስቲያን የታሪክ መዝገብ ተሰንዶ የሚቀመጥ አሳዛኝ ጠባሳ አስቀምጠዋል።



























